የፍ/ባለዕዳው አቶ አዲስ አየለ የሆኑ መኪኖች በ6/09/2017 ከ3:00 እስከ 6፡00 ባለው ሰዓት ውስጥ በግልጽ ጨረታ ተሸጦ ውጤቱ በ7/09/2017 በ4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ችሎት አዟል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
ጨረታ ማስታወቂያ
የፍ/ባለዕዳው አቶ አዲስ አየለ የሆነው ሰሌዳ ቁጥራቸው AA-03-A96258 እና AA-03-A99885 ከሆኑት መኪናዎች ውስጥ 1ኛ የሰሌዳ ቁጥር AA-03-A96258 የተሰራው በጃፓን ሀገር፤ በቶዮታ ፋብሪካ፣ አውቶሞቢል እስከ 4 ሰዎች መጫን አቅም ያለዉ፤ የዲክላራስዮን ቁጥሩ 697.379 የሆነ የተመረተበት ዘመን 2010 የሆነ የመነሻ ግምቱ 1,161,926.56 (አንድ ሚልዮን አንድ መቶ ስልሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ ስድስት ከ56/100) ፣ 2ኛ የሰሌዳ ቁጥር AA-03-A99885 የተሰራው በጃፓን ሀገር በቶዮታ ፋብሪካ፤ አውቶሞቢል እስከ 4 ሰዎች መጫን አቅም ያለው፤ የዲክላራስዮን ቁጥሩ GIMIT MASAWEK 600,00 የሆነ የተመረተበት ዘመን 2010 የሆነ የመነሻ ግምቱ 1,019,151.74 (አንድ ሚልዬን አስራ ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ 74/10 በ6/09/2017 ከ3:00 እስከ 6፡00 ባለው ሰዓት ውስጥ በግልጽ ጨረታ ተሸጦ ውጤቱ በ7/09/2017 በ4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ ታዘዋል፡፡
ስለዚህ ይህን መኪና በጨረታ ለመግዛት የሚፈልጉ ሰዎች
1ኛ. ለመግዛት የሚፈልጉትን መኪና ግምት 1/4ኛዉን በስንቄ ባንክ አሲዛችሁ ለጨረታዉ መመዝገብ ትችላለችሁ፡፡
2ኛ ተጫራቾች ለመወዳደር በሚመጡበት ጊዜ የታደሰ መታወቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባቸኋል፡፡
3ኛ ጨረታዉን የሚያሸንፍ ሰው ቀሪዉን ገንዘብ ፍ/ቤቱ በሚሰጠዉ ጊዜ ገደብ ውስጥ አጠናቆ ማስገባት የሚችል መሆን አለበት፡፡
4ኛ ጨረታዉ የሚከፈተዉ የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዋናዉ ጽ/ቤት ውስጥ በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰዓት ነዉ፡፡
5ኛ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲወጣ ታዟል፡፡
6ኛ ሁለቱም መኪኖች የተለያዬ የመነሻ ግምት ዋጋ ያላቸዉ ስለሆኑ ለብቻቸዉ ወይም አንድ ላይ መጫረት የሚቻል ሲሆን ይህን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምስራቅ ችሎት
