Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ዋናው መስሪያ ቤት አራት ኪሎ አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Phone: 0111555230
  • Websitehttps://ethbspe.org/en_US/
  • Deadline27 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-27 00:00:00
  • Categories Services , Machinery , Stationery Materials

ድርጅታችን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ አንድ (ሎት 1) - Yellow Balacron 70x100cm 350gm ብዛት 5,000 ቅጠል እና Grey Balacron 70x100cm 350gm 1 5,000 ቅጠል ግዥ፤

በጨረታ ሁለት (ሎት 2)- በድርጅታችን የህትመት ፍላሽ ኬሚካል ማጣሪያ የሚያገለግል ማሽን (Waste Water Treatment machine) ብዛት አንድ ለመግዛት የሚያስፈልግ ስፔስፊኬሽን፤ የማወዳደሪያ ነጥቦች እና የተሟላ የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት የአገልግሎት ግዥ (ተወዳዳሪዎች በድርጅታችን ዋናው መ/ቤት በመገኘት ቦታውን በአካል መመልከት ይኖርባቸዋል)፣

በጨረታ ሶስት (ሎት 3) - የረቂቅ ጽሑፍ ግዥ (ድርጅታችን ለገበያ ለሚያቀርባቸው አጋዥ መጻሕፍት የረቂቅ ሥራ)፤

በጨረታ አራት (ሎት 4) - አጋዥ መጻሕፍት የአርትኦትና ግምገማ ስራ አገልግሎት ግዥ (ድርጅታችን ለገቢያ ለሚያቀርባቸው አጋዥ መጻሕፍት የአርትኦትና ግምገማ ስራ የአገልግሎት ግዥ)፤

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሻል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ለሎት 1 እና ለሎት 2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒአ) ማስያዝ አለባቸው::

ጨረታው በ19/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30

ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)

Berhanena selam printing enterprise

 

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

 

Save Tender