Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-26 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የፍ/ባለመብት አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ጥሩነሽ ሀይሉ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 158630 በ28/6/2016 ዓ.ም እና መ/ቁ 160746 በ20/7/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቀድሞ የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 በአሁኑ ለሚኩራ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 1083 የሚገኝ ቦታ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ በሐራጅ ይሸጣል፡፡


 

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የፍ/ባለመብት አጋር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ጥሩነሽ ሀይሉ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 158630 በ28/6/2016 ዓ.ም እና መ/ቁ 160746 በ20/7/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቀድሞ የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 በአሁኑ ለሚኩራ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 1083 የሚገኝ ቦታ ስፋት 422 ካ/ሜ የባለሙያ ግምት 18,336.768 (አስራ ስምንት ሚሊዬን ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺ ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሔሴ 27 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች ያልቀረበ በመሆኑ ጨረታው ተቋርጧል ፡፡ በዚህ መሰረት ለፍ/ቤት ተጽፎ ፍ/ቤቱ በ19/7/2017 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ በድጋሚ እንዲወጣ ባዘዘው መሰረት መጫረት የሚፈልግ የግምቱ 1/4 ብር 4,584,192 (አራት ሚሊዬን አምስት መቶ ሰማንያ አራት ሺ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ብር በማስያዝ መጫረት የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender