በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የማባዣ ማሽን ቀለም MX-561FT For use Sharp ብዛት 10 በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ሶስተኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የማባዣ ማሽን ቀለም MX-561FT For use Sharp ብዛት 10 በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘርፍ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፡፡
- ክሊራን፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ፍቃድ ስለመመዝገባቸው (online registration) ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 7፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በትምህርት ቤቱ ስም (Temenja Yazh G/Secondary School) በተጠቀሰው ሎት ሰባት መቶ ሀምሳ ብር (750) በCPO የጨረታ ማስከበሪያ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች በቀጥታ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ 15% VAT ጨምሮ የመሙላት ግዴታ አለባቸው ይህን ያላደረጉ ተጫራቾች ቫትን አካተው እንደሞሉ ይቆጠራል፡፡
- በእያንዳንዱ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወይም ገፅ ወይም ሎት ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ክብ ማህተም እና ፊርማ በማኖር ማስገባት ይኖርባቸዋል ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ህጋዊነቱን እና ኦርጅናልነቱን ለመለየት ስለማያስችል ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች በከፊል ወይም በሎት ወይም በገፅ ወይም ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ፋይናሺያሉን ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና የፋይናሺያሉን ኮፒ በሌላ አንድ ተጨማሪ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካሉን ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ በአጠቃላይ በሶስት ፖስታ ብቻ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ይህን ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና በጨረታ ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያው ቦታ ላይ የተሞላ መሆን አለበት ይህ ካልሆነ መስሪያ ቤቱ ስርዝ ድልዝ ያለበት እና በውል ለመለየት አዳጋች የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ወይም ሎት ወይም ገፅ በከፊል ውድቅ ያደርገዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና በሚያስፈልጋቸው እቃዎች ማለትም የማባዣ ማሽን ቀለም MX-561FT For use Sharp ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የፍላጎት መግለጫ ውጭ የሚቀርቡ የናሙና ዓይነቶች ድርጀቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ ማናቸውም ዓይነት ናሙና ድርጅቱ ሊቀበል አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር ስምንት (08) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ውል በገቡ በሰባት የስራ ቀን ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፦ ጠመንጃ ያዥ የባቡር ፌርማታው ፊትለፊት በእምነት ባርና ሬስቶራንት በስተጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114703870 ይደውሉ፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጠመንጃ ያዥ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
