Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-44-83-714
  • Website
  • Deadline29 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-29 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እና ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር (0013/2017)

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች እና ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  • በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ማንኛውም የድርጅት ተወካይ ወይም ግለሰብ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ጨረታውን በመካፈል መሳተፍ ይችላል።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከማከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30-6፡00 እና ከሰዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡30-6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ተሸከርካሪ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ከ16/8/2017 እስከ 21/8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት ተሽከርካሪዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ21/8/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የጨረታው መክፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ በ5 ቀናት ውስጥ ተሸከርካሪዎቹን ተረከበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ተሸከርካሪዎቹን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ተሸከርካሪዎቹን በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
  •  ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ 057-44-83-714 ደውስው መጠየቅ ይችላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender