Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
  • Address Ethiopia Kombolcha City, Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0116730520
  • Website
  • Deadline29 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-29 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Vehicle Battery , Construction Vehicle

በጉምሩከ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ LED LGHT ALLUMINUM PROFILE ፕላፕሌት፣ የድንኳን ሸራ ፣ ኮስሞቲክስ ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ ቻርጀር ፒን እና ሎደር በግልጽ እንዲሁም COOKIES MACHNE ፤ ተሽከርካሪ ፣ ቻርጀር ፒን ሪሞት ኮንትሮል፣ ሻምፖ እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


 

የጨረታ ማስታወቁያ

ጨረታ ቁጥር 24/2017 ዓ.ም

 

በጉምሩከ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ LED LGHT ALLUMINUM PROFILE ፕላፕሌት፣ የድንኳን ሸራ ፣ ኮስሞቲክስ ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ ቻርጀር ፒን እና ሎደር በግልጽ እንዲሁም COOKIES MACHNE ፤ ተሽከርካሪ ፣ ቻርጀር ፒን ሪሞት ኮንትሮል፣ ሻምፖ እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቶች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛም ከ18 አመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡
  2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋዉ ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡
  3. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጉምሩክ ገቢ ሂሳብ ቡድን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛ (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በስድስተኛ ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልጽ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ-05 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  8. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በስድስተኛ ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና በስድስተኛ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ እቃዎች መቶ ሺህ ብር (100,000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender