በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለጹትን ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 08/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለጹትን ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
No. |
Items |
Quantity |
|
1 |
Dump truck |
2 |
|
2 |
Tractor |
1 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት /Tin Number/ ያላቸው
- ግብር ለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ በተሸከርካሪ አይነት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 30ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በሚወዳደሩበት በየተሸከርካሪ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-10-92-89-86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
