በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ 1 በዕርዳታና በስጦታ ያገኟቸኛ ያገለገሉ ንብረቶችን መጽሐፍቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ወረዳው በተለያዩ ጊዜ በግዥ 1 በዕርዳታና በስጦታ ያገኟቸኛ ያገለገሉ ንብረቶችን መጽሐፍቶች እና ሌሎች ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ መስፈርቶች፤
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ፣
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ከወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና አንድ የኦሪጅናል ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከገዙ በኃላ ከጨረታው ቀን በፊት በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ግቢ በመድረስ ንብረቱን በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፉትን ዋጋ በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ መደበኛ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያኑ ይረከባል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነዱ የሚካተቱ ይሆናል፡፡
- የሞተር ተሽከርካሪዎች ስም ዝውውር በገዢ ይሸፈናል፤ የተሽከርካሪዎች ማስረጃ መ/ቤቱ ለገዥው ያቀርባል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ዉሎ ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር :- 09-16-59-96-57/09-16-35-11-13/09-25-14-75-81 ይደውሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
