በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ መድሐኒቶች ፣ ሪኤጄንቶች ፣ ህክምና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 03/2017
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
1. መድሐኒቶች፣ ሪኤጄንቶች፣ ህክምና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል በአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ ለመሆኑ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አንድ አንድ ናሙናዎችን የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ቃሊቲ ቼራሊያ አለፍ ብሎ አቢሲኒያ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የሚወዳደሩበትን ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑና የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት መድሀኒቶች ፣ የህክምና ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ 300,000.00 ብር
- በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ብቻ ሲሆን በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማቅረብ የሚችል መሆኑን፡፡
- ተጫራቾች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ (Specification) ሰነድ ላይ መሙላት አለባቸው።
በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞሉ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹ ገፅ ላይ ማህተም በማድረግ እና የዋጋ መሙያው (specification) ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በጥንቃቄ በመሙላት ፊርማና ማህተም መደረግ አለበት፡፡
- ተጫራች ጨረታ ሰነዳቸውን ኮፒ እና ኦርጂናል በማለት በሁለት ፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን በአየር ላይ ከዋለ ተጫራች ጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ጨረታው በአየር ላይ በዋለ 10 ቀን ውስጥ ዘወትር በሥራ ቀናት ቸራሊያ አለፍ ብሎ አቢኒያ ህንጻ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ11ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በመያዝ ቀርበው ውል መዋዋል አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ግልጽ ያልሆኑ መረጃዎች ካሉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0118696056 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
