Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ከሚሴ
  • Address ከሚሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335541737
  • Website
  • Deadline10 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-10 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የማንጎ እና የአቮካዶ የአካባቢ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ከሚሴ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ለ2017/2018 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የማንጎ እና የአቮካዶ የአካባቢ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ያለዉን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ 1-የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ የመንግስት ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን ቁጥር/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  3. ከዕጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ኳራንቲን ባለስልጣን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  4. ዘሩን ሲያቀርቡ የዘሩን ጥራት ከግብርና ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ኳራንቲን ባለስልጣን የደህንነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  5. ዘሩን በሚፈለግበት ወቅት ግዥ ከተፈጸመበት ቦታ እስከ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞንና በዞኑ ስር ባሉ ወረዳዎች ዘሩ ለሚቀርብላቸው ችግኝ ጣቢያዎች ድረስ ማቅረብ የሚችል
  6. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የአገልግሎት ዋጋ 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአብክመ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ግብርና መምሪያ ስም በመክፈል ከዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
  7. የመጫረቻዉን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ/መሞላት ይኖርበታል እንገልፃለን፡፡
  8. ተጫራቶች ስለ ዘሩ ዝርዝር ሁኔታ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነድ ዉስጥ ያገኛሉ
  9. ስርዝ ድልዝ ያለዉ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረዉም
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /መቶ ብር/ ከፍለዉ ከዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መመሪያ ማግኘት ይችላሉ ::
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ኦሮሞ ዞን ግብርና መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሠነድ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 4፡01 ተዘግቶ የሚከፈተው በእለቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛ ቀን የመንግሰት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የመንግስት የሥራ ቀን 4፡01 ተዘግቶ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ የግዥ ዉል እንዲፈጽም ከመ/ቤት ደብዳቤ በደረሰዉ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መግባት ይጠበቅበታል።
  13. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በተዘጋጀዉ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት ዋናዉንና ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የድሮው አስተዳደር ህንጻ አንደኛ ፎቅ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0335541737/091245390 7/0910172480 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮ/ዞን ግብርና መምሪያ ከሚሴ

 

Save Tender