በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ የተለያዩ የወርክሾፕ መሣሪያዎች (Floor Jack, Tyre Changer for Heavy Truck, Air Compressor, Arc Welding Machine, Waste Oil Drain Collector Machine) በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጥገና ዘርፍ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ተአጥዘ/ግጨ/02/2017
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ የተለያዩ የወርክሾፕ መሣሪያዎች (Floor Jack, Tyre Changer for Heavy Truck, Air Compressor, Arc Welding Machine, Waste Oil Drain Collector Machine) በተቀመጠው መመሪያና ግዴታዎች መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች መጫረት ይችላል፡፡
- የግዥ ፈፃሚ አካል ስም:- በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ
- የዕቃው ዓይነት:-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-
- አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ኮፒውን በማቅረብ ዋናውን ሲጠየቁ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የቴክኒክ መወዳደሪያ ሠነድ ከተከፈተ በኋላ በቴክኒክ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች የተወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት በክምችት እንዳላቸው ይህንን ዕቃ ለማየት ለሚመጡ የኮሚቴ አባላት ማሳየት ይኖርባቸዋል። በተለያዩ ምከንያት ሳያሳዩ ቢቀሩ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቃሊቲ የተሽከርካሪ አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ በሚገኝው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ዕቃ የአጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ (CPO) ሲያዘጋጅ
- በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ አስተዳደር ጥግና ዘርፍ ስም መዘጋጀት አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን:- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዝግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀናት እንዲሁም የዕረፍት ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራች በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ሳይጎኝ ቢቀር የጨረታው መከፈት ሂደት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የተለያዩ የወርክሾፕ መሣሪያዎች (Floor Jack, Tyre Changer for Heavy Truck, Air Compressor, Arc Welding Machine, Waste Oil Drain Collector Machine) የሚጫረቱበትን ዋጋ በግልፅ እንዲሁም በሚታይና ግልፅ በሆነ መንገድ ከስርዝ ድልዝ በፀዳ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና (original እና እንድ ቅጂ (copy) ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግና በመፈረም የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ አድራሻ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡30-11፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቃሊቲ በሚገኝው የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ሳጥን ውስጥ ከመግባቱ በፊት መመዝገብ ይኖርቦታል።
- የጨረታ ሰነዱን ሳይገዛ የተጫረተ ማንኛውም ድርጅት ከተገኘ ከጨረታው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ዘርፉ ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡር መጨረሻው ጣቢያ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ጀርባ ገባ ብሎ ግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት 100 ሜትር ገባ ብሎ ግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ግቢ ውስጥ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ጥገና ዘርፍ
