Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 011 681 3410
  • Website
  • Deadline07 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-07 00:00:00
  • Categories Vehicle Battery , Used Items

በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው ጐማዎች ያገለገሉ፤ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ በርሜሎች፤ የተቃጠለ ማለስለሽ ዘይትና ሌሎች አሮጌ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2017

 

በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት ያገለገሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው ጐማዎች ያገለገሉ፤ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ በርሜሎች፤ የተቃጠለ ማለስለሽ ዘይትና ሌሎች አሮጌ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ግለሰቦች፣ ማህበራትና ድርጅቶች መሣተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በጨረታው ዙሪያ ሊከተሉዋቸውና ሊያውቋቸው የሚገባቸው ጉዳዮች

  1. ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ፤ማህበራትና ሌሎች ፍላጎት ያላቸው አካላት በጨረታው የመሣተፍ መብት አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/በመክፈል ሰ/ሸዋ ገ/መ/ጥ/ጽ/ቤት ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት /መግዛት/ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ላይ የሚሸጡትን ያገለገሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ጐማዎች ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች ያገለገሉ በርሚሎች የተቃጠሉ ዘይቶችና እንዲሁም ሌሎች እቃዎች አይነትና መጠን ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ያገለገሉ ጐማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣አሮጌ በርሜሎችና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ዝርዝር መሰረት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ይህም ማለት ውድድሩ በጥቅል ድምር እንደሆነ ለመግለጽ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት ንብረቶች ውስጥ በተናጠል ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  8. ተጫራቾች አሸናፊነት በተገለፀበት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፋበትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ንብረቱን ማንሣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ካልሆነ መ/ቤቱ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ ወደ ሁለተኛው አሸናፊ የመሄድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች ንብረቶቹ ባሉበት ቦታ ማለትም ጠባሴ በሚገኘው የሰ/ሸዋገ/መ/ጥ/ጽ/ቤት/ ደ/ብርኃን ድረስ በመምጣት በአካል መመልከት ይችላሉ፡፡
  10.  ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  11.  የጨረታ መክፈቻው በባዕል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12.  መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13.  ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 681 3410/ 011 681 3066 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት

 

Save Tender