የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሃዋሳ ኤርፖርት ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የምግብ አይነቶችን (አትክልትና ፍራፍሬ፣ የሱፐር ማርኬት እቃዎች፣ የሥጋ ምርት፣ የስንዴ ዱቄት፣ የጤፍ ዱቄት) በጨረታ አወዳድሮ ለ3 (ሶስት) ዓመት በሚቆይ የውል ጊዜ ማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T535
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሃዋሳ ኤርፖርት ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የምግብ አይነቶችን (አትክልትና ፍራፍሬ፣ የሱፐር ማርኬት እቃዎች፣ የሥጋ ምርት፣ የስንዴ ዱቄት፣ የጤፍ ዱቄት) በጨረታ አወዳድሮ ለ3 (ሶስት) ዓመት በሚቆይ የውል ጊዜ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፤
- በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ ለ2017 የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN ምዝገባ ወረቀት) ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው
- ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNI-I535 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 25,000 /ሀያ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን ከታች በተቀመጠው አድራሻ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል በሚገኘው የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-4552
አሊ አስፋው
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
