የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የማዉንት ክሬን ትራክ ኪራይ 10 ቶን መሸከም የሚችል ለአንድ አመት የሚቆይ የማእቀፍ ስምምነት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Water and Sewerage Authority (የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡-NCB/GOV/AAWSA/N-C-S001/2017
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የማዉንት ክሬን ትራክ ኪራይ 10 ቶን መሸከም የሚችል ለአንድ አመት የሚቆይ የማእቀፍ ስምምነት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 113 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ፣ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ ብር 20,000 /ሃያ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ቴክኒክ ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን በሁለት ፖስታ (Two envelopes) /የቴክኒክ እና የፋይናንሺያል (ዋጋ) ለየብቻ ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በመለየት የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳዳሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት።
ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
- ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
