የጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠማቸውን ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች በእስፔር ፓርትነት መገልገል ለሚፈልግ ድርጅት/ግለሰብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋናንስ ጽ/ቤት
ያገለገሉ ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መ/ቁጥር 002/2017
የጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠማቸውን ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች በእስፔር ፓርትነት መገልገል ለሚፈልግ ድርጅት/ግለሰብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ ፤ የግብር ከፋይነት ያሟላችሁና የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፣
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ጨረታውን ሰነድ ከእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማሰራት አለባችሁ፤
- የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል፤
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎችን ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢው በመገኘት ማየት ይችላሉ፤
- ተጫራቶች ንብረቱን ለመግዛት በሙሉም ሆነ በከፈል ዋጋ መሙላት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች አርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ በኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፤
- ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይተላለፋል፤
- ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ቢድ ቢንድ ከሆነ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- የተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች የሕይወት ታሪክ የሌላቸው በመሆኑ የስም ዝውውር የለውም ስለዚህ በእስፔርፓርትነት የሚሸጡ መሆኑን እናሳውቃለን፤
- ማስታወቂያው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሚጋብዝ ቢሆንም ሌሎች ማንኛውም ፈቃድ የሌለው ግለሰብ መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፤
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0944020662/0911077093
የጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
