የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ
ቁጥር EEP/ST/NCB/23/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ በሚመለከተው ኃላፈ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሠነዱ ውስጥ ያገኛሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ብሎክ አስራ አንድ (11) 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112 ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ብሎክ ዘጠኝ 1ኛ ፎቅ ስታፍ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/23/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው አይነት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ |
50,500.00 (ሃምሳ ሺህ አምስት መቶ ብር) |
ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
- ግዥ ፈጻሚው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
