የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ በርሜሎች እና ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፤ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ በርሜሎች እና ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ኘላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው::
- ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር (መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ በርሜሎች፣ እና ሌሎችም የአንዱን መስሪያ ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች፣ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን እከፋፈት እያስተጓጉልም፡፡
- አንድ ተጫራች ከአንድ የመንግስት ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
- በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
