ቱምሣ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ ያገለገሉ መኪኖችን በጨረታ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡
ቱምሣ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ
የጨረታ ማስታወቂያ
ቱምሣ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ ያገለገሉ መኪኖችን በጨረታ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡
ስለሆንም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራFF ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
- ኢትዮጵያዊ የሆነ እና የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት፤
- የንግድ ፍቃድ ያለው እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ወይም ያላት፤
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንፃ 10ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡00 እሰከ 11:00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈረም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የእያንዳንዱን መኪና መነሻ ዋጋ 10% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታ በሥራ ሰዓት ማየት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መከፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 10ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-113-52-75
ቱምሣ ዲቬሎፕመንት ግሩፕ
