Tender Detail

Tender Details

  • Company የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ቢሾፍቱ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-437-16-83
  • Website
  • Deadline30 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-30 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot.1 A4 Computer paper በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot.1 A4 Computer paper በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው::
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቶች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር (10) ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡
  5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (cpo) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ15 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
  11. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም
  12. ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይንንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender