በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሶዶ ሃገረ-ስብከት የማህበራዊና ልማት ማስተባበርያ ጽ/ቤት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሰረቱን በኢትዮጵያ ያደረገ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች (ዳሰነች እና ኛንጋቶም) በተመረጡ 17 ቀበሌያት የሶስት አመት የልማት መርሃ ግብር (ፕሮጄክት) ቀርጾ ወደ ተግባር የገባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው 17 ቀበሌያት ውስጥ ለፍየል ድጋፍ ለተመረጡ 200 ተጠቃሚዎች 1000 ፍየሎችን እንድያሞክቱ ለተጠቃሚዎች ገዝቶ ለማቅረብ ይፈልጋል::
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሶዶ ሃገረ-ስብከት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሶዶ ሃገረ-ስብከት የማህበራዊና ልማት ማስተባበርያ ጽ/ቤት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መሰረቱን በኢትዮጵያ ያደረገ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች (ዳሰነች እና ኛንጋቶም) በተመረጡ 17 ቀበሌያት የሶስት አመት የልማት መርሃ ግብር (ፕሮጄክት) ቀርጾ ወደ ተግባር የገባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው 17 ቀበሌያት ውስጥ ለፍየል ድጋፍ ለተመረጡ 200 ተጠቃሚዎች 1000 ፍየሎችን እንድያሞክቱ ለተጠቃሚዎች ገዝቶ ለማቅረብ ይፈልጋል:: በዳሰነች ወረዳ (ቡቡኣ፤ አሪኮል እና ሰለኝ) በኛንጋቶም ወረዳ (ኩቹሩ፣ ካኩታ እና ናፕቶኮይት) በአጠቃላይ 6 ቀበሌያት ውስጥ የምሰራጩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለአመቱ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀቶች ቅጂዎች በማቅረብ በጫረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል:: ስለሆነም ፡
- ጨረታው ክፍት በሆነ የአከባቢ ጨረታ አሰራር ይፈጸማል::
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሶዶ ሃገረ-ስብከት የማህበራዊና ልማት ማስተባበርያ ጽ/ቤት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በድርጅቱ ስም በኢትዮ. ንግድ ባንክ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000329846109 በማስገባትና የከፈሉበትን የባንክ ገቢ ደረሰኝ በማምጣት ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሶዶ ሃገረ-ስብከት የማህበራዊና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኦሞራቴ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ መጠን 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ሁሉም ተጫራቾች አንድ ኦሪጅናል ምልክት የተደረገበት “ኦሪጅናል'' እና አንድ ቅጂ ልክ እንደ መጀመሪያው በተመሳሳይ መልኩ የተፈረመ እና ርዕሱን በመግለጽ “ኮፒ" የሚል ምልክት የተደረገበት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጣበት በ8ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ገብቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው::
መ/ቤቱ
