የሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለኮሪደር መንገድ መሰረት ልማት ሥራ የሚውል ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሆለታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለኮሪደር መንገድ መሰረት ልማት ሥራ የሚውል ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሮት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የያዘና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበና ሰርተፍኬት ያለው፤
- ተጫራቾች ካወጣችሁት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ የተወዳደረ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 100000 (መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 /100 በባንክ ማስያዝ የሚችል፤
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፤
- መስሪያ ቤቱ ለሚጠረጥራቸውና ማጣራት ለሚፈልገው ዕቃ ናሙና ማስቀረብ ይችላል፤
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይየሥራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው በ8፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ከሆለታ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ትችላላችሁ፡፡
ማሳሰቢያ-
-
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-
0112370095/ 0911045695/ 0913445227/ 0913469364 መጠየቅ ትችላላችሁ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
