በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ለእንስሳት ዘርፍ አገልግሎት የሚውል የእንስሳት መድሀኒት እና መገልገያ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አካላቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወያቂ
ቁጥር 10/2017
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ለእንስሳት ዘርፍ አገልግሎት የሚውል የእንስሳት መድሀኒት እና መገልገያ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አካላቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈለ ፣ እና ስለመከፈሉ የገቢዎች ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ጨረታው የሚቆየው ከ7/8/2017 ዓ.ም እስከ 21/8/2017 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በሁለት ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በመሙላት ሶ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 4 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 21/8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በ9፡00 ሰዓት ሶ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት የግ/ክ/ን/አስ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO 10000 /አስር ሺህ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈፅም በግዢ መመሪያ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል ፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሰረት አሸናፊ የሆኑባቸው መድሀኒቶችና እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ፋይናንስ ጽ/ቤት ንበረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች የመድሀኒትና እቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላል ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0468830128
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
