በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተሸከርካሪ ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተሸከርካሪ ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ዋ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል። ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ፣ ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒአ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት።
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፈርማ ማረፍ አለበት።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሽነፉበትን ጎማዎች ጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኋላ ለ3 ወር ማለትም ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0461310108 መደወል ይችላሉ፡፡
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት
