የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የዲጂታል ሜትር የታክሲ አገልግሎት አቅራቢ እና አስተዳደር ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማስራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T534
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የዲጂታል ሜትር የታክሲ አገልግሎት አቅራቢ እና አስተዳደር ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማስራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በተጠቀሰው አገልግሎት ዘርፍ ላይ ቢያንስ ሦስት (3) ዓመት የሰራ ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያለውና በዘርፉ እየሰራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T534 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል::
ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
በስልክ ቁጥር 011 517 8025
ኢ-ሜይል: eskedarya@ethiopianairlines.com
