በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛና በሌሎች በጀት ከዚህ በታች የተገለጸውን የተሽከርካሪ ጎማ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
South Ethiopia Regional State Water, Mines And Energy Bureau (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛና በሌሎች በጀት ከዚህ በታች የተገለጸውን የተሽከርካሪ ጎማ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የተሽከርካሪ ጎማ
ከዚህ በላይ ለተገለፁት እቃዎች በውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሠነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፤30 ድረስ የሚያስገቡና የሚታሸግ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 9፣00 ሰዓት ይከፈታል፤
- ይህ እንዳለ ሆኖ 15ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤
- ከላይ ከሎት 1 የተገለጸው የጠቅላላ ሽያጭ ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ሲሆን የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ/ ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታው ለአንድ ወራት 30 (ሰላሳ) ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፤
- አሸናፊው ተጫራች ጎማዎቹን ለማቅረብ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያና ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፤
- የጨረታ ሰነዱን ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች በጨረታ በሎት በቀረበው ድምር የጎማዎች ዋጋ ላይ ከ2% በመብለጥም ሆነ በማነስም የቀረበ ድምር ስህተት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፤
- ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ማሳሰቢያ ፡-
ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺ/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ የቫቱን 50% ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን አንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0461310243/0904770435 ደውለው ይጠይቁ
አድራሻ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ዲላ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
