Tender Detail

Tender Details

  • Company በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት
  • Address ጅማ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0471180256
  • Website
  • Deadline24 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-25 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ከዚህን በፊት በወረዳው ውስጥ የገጠር መንገድ ተደራሽነት (URRAP) ፕሮግራም ተሰርተው የነበሩትን የገጠር መንገዶች እና አዲስ የመንገድ ስራ በ2017 ዓ/ም በሕዘብ ተሳትፎ በጀት እና በ ወረዳው በጀት ከቴሌ- መሳ 20ኪሜ ጥገና ፣ አንጃ-ቶሊ ጋሳራ ጥገና 8 ኪ.ሜ፣ አንጃ -ገምቦ ሚጊራ 9 ኪሜ ጥገና እንዲሁም አትሮገፈሬ-ኮሞ 6 ኪ.ሜ ጠጠር ማንጠፍ ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ከዚህን በፊት በወረዳው ውስጥ የገጠር መንገድ ተደራሽነት (URRAP) ፕሮግራም ተሰርተው የነበሩትን የገጠር መንገዶች እና አዲስ የመንገድ ስራ በ2017 ዓ/ም በሕዘብ ተሳትፎ በጀት እና በ ወረዳው በጀት ከቴሌ- መሳ 20ኪሜ ጥገና ፣ አንጃ-ቶሊ ጋሳራ ጥገና 8 ኪ.ሜ፣ አንጃ -ገምቦ ሚጊራ 9 ኪሜ ጥገና እንዲሁም አትሮገፈሬ-ኮሞ 6 ኪ.ሜ ጠጠር ማንጠፍ ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ለዚሁ ሥራ የሚሆን ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሻወር ትራክ እና የሲኖትራክ ገልባጭ መኪና (16 M3) ባለንብረቶችን የወረዳው ገ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

  • ህጋዊ የአከራይ ፍቃድ ያለዉ::
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ያሳደሰ::
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል::
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ብር /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረዳው ገ/ጽ/ቤት በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ የሚችል ::
  • ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ የሚዘጋበት ቀን በአስረኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ፡- የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 0471180256

 

 

በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት

 

Save Tender