Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት
  • Address ደብረሲና ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116800478
  • Website
  • Deadline28 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-28 00:00:00
  • Categories Water Pipes And Fittings

የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለውሃ አገልግሎቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት


 

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለውሃ አገልግሎቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በየሎቱ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ሎት 1 የብረት ቧንቧ፣ የብረትና የፕላስቲክ ቧንቧ መገጣጠሚያዎች በተናጠል ግዥ :

በዚህ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ::

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የሚሞላው የዕቃ ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ያላቸው፤
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በሎት1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነዱ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በደብረሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት ቢሮ 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ CPO ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ::
  8. ተጫራቹ በሎት 1 ያሉትን ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ፣ ስም ፊርማ እና አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በደብረሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ሎት ጽ/ቤት በግ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጽ/ቤታችን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116800478/ 0920856115/በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  11. ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ሳምፕሎቹን ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች በውድድር የማይሳተፍ መሆኑን ጽ/ቤቱ ያሳውቃል::
  12. ለዋና መስመር፣ ለአነስተኛ እና ለመካከለኛ የውሃ ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል የብረት ቧንቧ፣ የብረት እና የፕላስቲክ ቧንቧ መገጣጠሚያዎች ዕቃዎች /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል።
  13. ለበለጠ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይቻላል።

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የደ/ሲና ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት

 

Save Tender