Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ምዕራብ ጎንደር : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0918 606 804
  • Website
  • Deadline27 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-27 00:00:00
  • Categories Construction Vehicle

በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን መሪ አማካኝነት የ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ከተማዎችና ቀበሌዎች ለልማት አገልግሎት የሚውል ሎደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


 

በአስቸኳይ የሚወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን መሪ አማካኝነት የ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ከተማዎችና ቀበሌዎች ለልማት አገልግሎት የሚውል ሎደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው፡፡
  2. ግብይቱ ከ 200000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  3. ከሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት ስርዝ ድልዝ ካለዉ በፊርማ መረጋገጥ አለበት። የሚያቀርቡት የንግድ ፍቃድ እና ቲን ነምበር ግልፅ እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  4. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራጮች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ገንዘብ መምሪያ/በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ፅ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን አማካኝነት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ 15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨራታ ማስከበሪያ ዋስትና /ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የዋጋዉን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናውን እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ፅ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 16ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በ16ኛው ቀን በ9፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11.  አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃ/አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መውሰድና ወደ ስራ መገባት አለበት፡፡
  12.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13.  በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/አ/ጫ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን መሪ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0918 606 804/0918 739 709 /0922 718 368 /058 284 0410/ ቁጥር የሚፈልጉትን ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈፃፀም ችግር ምክንያት የታገዱ ወይም የእቃ አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ተጫራቾች አይጋብዝም፡፡

 

የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender