Tender Detail

Tender Details

  • Company South West Ethiopia Roads Authority (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)
  • Address Ethiopia, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline26 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-26 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Construction Vehicle

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ ጨረታ በቦንጋ ዲስትሪክት ቦንጋ አድያ-ካካ ሎት1 መንገድ ጥገና ለ2ኛ ጊዜ በወጣ ጨረታ በሚዛን ዲስትሪት ኩካ ካሚና እና ሸኮ-ኢተቃ መንገድ ጥገናዎች እንዲሁም ለ3ኛ ጊዜ በወጣ ጨረታ ቦንጋ ዲስትሪክት ዳካ-ሳይለም ሎት 1 መንገዶችን ለማስጠገን ገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

South West Ethiopia Roads Authority (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን)


 

ለ1ኛ፤ 2ኛ እና 3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 012/2017

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣ ጨረታ በቦንጋ ዲስትሪክት ቦንጋ አድያ-ካካ ሎት1 መንገድ ጥገና ለ2ኛ ጊዜ በወጣ ጨረታ በሚዛን ዲስትሪት ኩካ ካሚና እና ሸኮ-ኢተቃ መንገድ ጥገናዎች እንዲሁም ለ3ኛ ጊዜ በወጣ ጨረታ ቦንጋ ዲስትሪክት ዳካ-ሳይለም ሎት 1 መንገዶችን ለማስጠገን ገልባጭ መኪናዎችን ከነሎደሩ በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 በማስገባት ባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ::
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ከፍት ነው፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው በ16ኛ ቀን 3:00 ተዘግቶ በዛው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
  6. ተጫራቶች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) በየሎት ለይተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ ሁለት የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ - ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 0474527727 ደውለው ማነጋገር ይቻላል፡፡

 

 

ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ኢትዮጵያ

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን

Save Tender