ድርጅታችን ሰላም የጤና ማዕከል ኃላ/የተወ/የግል/ማኅበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎችን መካኒሳ ቆሬ አደባባይ በሚገኘው ቢሮአችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሰላም የጤና ማዕከል ኃላ/የተ/የግል/ማኅበር
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ሰላም 003-17
ድርጅታችን ሰላም የጤና ማዕከል ኃላ/የተወ/የግል/ማኅበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎችን መካኒሳ ቆሬ አደባባይ በሚገኘው ቢሮአችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- 59 ሰው የሚጭን ሬኖልት አውቶቡስ
- ኦፔል ኮርሳ የቤት አውቶሞቢል
- ቫን ሚኒ ባስ
- ቫን አምቡላንስ
- ኦፔል አስትራ የቤት አውቶሞቢል
የጨረታው መመሪያዎች፡-
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ከፍለው በመግዛት ወይንም በድርጅቱ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000557384395 ገቢ አድርገው ደረሰኙን በማቅረብ መካኒሳ ቆሬ አደባባይ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ተሸከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ በመለየት ለአንድ ጨረታ የቀረበውን በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ሰነድና ተሽከርካሪውን የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ ፎርሙ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተገቢውን ሰነዶች ካሟሉ በኋላ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ሰዓት ዋናው መሥሪያ ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው እሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ተሳታፊ ሆነው ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙትን ገንዘብ (BID BOND) ውጤቱ ከተገለጸ ከ3 ቀናት በኋላ ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የስም ማዛወሪያና በሽያጩ ምከንያት የሚጣለውን ማናቸውንም የመንግሥት ግብር፣ ቀረጥ፣ የቴክኒክ ምርመራና ቦሎ፤ በመንገድ ትራንስፖርት በኩል የሚጠየቀውን የተሽከርካሪውን የሽያጭ ግምት ክፍያ እንዲሁም የማናቸውንም ተዛማጅ አገልግሎቶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በገዢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው በመፈጸም በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ወጪ ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ካላነሱ ለተከታታይ 5 ቀናት በየቀኑ የመጠበቂያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ፡፡
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቹ ያቀረበውን ዋጋ ከመነሻው ዋጋ አሳንሶ ወይም ስርዝ ድልዝ ያለው ሆኖ ከቀረበ ወዲያውኑ ውድቅ ይደረግበታል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
አድራሻ፡ መካኒሳ ቆሬ አደባባይ
ስልክ ቁጥር: 0911 656066/ 0911 314603
አዲስ አበባ
ሰላም የጤና ማዕከል ኃላ/የተ/የግል/ማኅበር
