የማዕከላዊ ክልል መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ክልል መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ዓይነት |
የዕቃው ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
ምርመራ |
|
1 |
ሎት 1 |
ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች |
100,000 |
በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ |
|
2 |
ሎት 2 |
የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር |
100,000 |
|
|
3 |
ሎት 3 |
የምግብ በቆሎ |
100,000 |
በዚሁ መሠረት ፡-
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉ እና በፋ/አ/ል/ቢሮ (በፋ/ኢ/ሚኒስቴር) በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
-
-
-
-
-
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘረውን የእያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለብቻ ለብቻ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማዕከላዊ ከልል መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት /CPO/ ከቴክኒካል ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሳቸው መ/ቤት በመምጣት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ጋራንቲ በማስያዝ ከቢሮው ጋር ውል መግባት አለባቸው::
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበት የዕቃ ዓይነት ዕቃውን በራሱ ማጓጓዣ ቢሮ ድረስ በማቅረብ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይፈራረም የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስገባው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
-
-
- ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ስትሞሉ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት፡፡ ካልሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነድ መረዳት ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-
-
-
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-31-09-01/ 09-16-78-41-14/ 09-89-98-04-72 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ማዕከላዊ ክልል መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሆሳዕና አሮጌው መናኸሪያ ጀርባ ዶ/ር ጳውሎስ የጥርስ ህክምና ህንጻ አንደኛ ፎቅ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
