በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ለዞኑ የመንግስት ሠራተኞች ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ 61.3 ወይም 61.D ወንበር የሚይዝ ባስ ምርት ዘመን 2021 እ.ኤ.አ እና በላይ አዲስ ዜሮ ዜሮ የሆነውን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት
ሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ለዞኑ የመንግስት ሠራተኞች ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ 61.3 ወይም 61.D ወንበር የሚይዝ ባስ ምርት ዘመን 2021 እ.ኤ.አ እና በላይ አዲስ ዜሮ ዜሮ የሆነውን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከላይ የተጠቀሰውን አይነት መኪና በጨረታ ለማቅረብ የሚችል ድርጅት ግለሰብ/ማሟላት ያለበት መስፈርቶች:-
1ኛ. የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ የሚችል፡፡
2ኛ. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ሠነድና ቴክኒካል ሠነድ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከዳውሮ ልማት ማህበር ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይቻላል፡፡
4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፈርት የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡
5ኛ. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 16ኛው ቀን ጨረታው ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን ብሔራዊ በዓላት ወይም ሰንበት ላይ ከዋለ ለቀጣዩ የስራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
6ኛ. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ በልማት ማህበሩ ስም በታወቀው ባንክ የተሰራ ሲፒኦ ብቻ/ ከቴክኒካል ሠነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
7ኛ. በጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝና የማይነበብ ካለ ተቀባይነት የለውም፡፡
8ኛ. ተጨማሪ ስለ ጨረታ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0473 45 02 58 /0917832352/ 0917832637 ይደውሉ፡፡
9ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የዳውሮ ልማት ማህበር
