Tender Detail

Tender Details

  • Company የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 047-3-45-02-58
  • Website
  • Deadline01 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-01 00:00:00
  • Categories Industry And Factory

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በዳውሮ ዞን የሚገኘው የዳውሮ ልማት ማህበር የድንጋይ ከሰል ምርት ሥራ ለማካሄድ አስፈላጊውን ፈቃድ ወስዶ ወደ ተግባር ለመግባት በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል፡፡

የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በዳውሮ ዞን የሚገኘው የዳውሮ ልማት ማህበር የድንጋይ ከሰል ምርት ሥራ ለማካሄድ አስፈላጊውን ፈቃድ ወስዶ ወደ ተግባር ለመግባት በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር አብሮ ለመሥራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርት አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1ኛ. በሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣

2ኛ. በዚህ ሥራ ዘርፍ የተሻለ ልምድ መኖሩን የሚገልጽ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል፣

3ኛ. በዚህ ሥራ ዘርፍ የቅርብ የ6 ወር እና ከዛ በላይ በፈቃድ ሰጪው አካል የተገመገመ ፊዚካልና ፋይናንሻል ሪፖርት ማቅረብ የሚችል፣

4ኛ. በድርጅቱ ልምድ ያለው የዘርፉ ባለሙያ ስለመኖሩ ከነቅጥር መረጃ ማቅረብ የሚችል፣

5ኛ. ድርጅቱ ሲያንቀሳቀስ የነበረው ቢያንስ 60,000,000.00 /ስልሳ ሚሊዮን ብር/ ድረስ የካፒታል አቅም መኖሩን የውጭ ኦዲት ሪፖርት ማቅረብ የሚችል፣

6ኛ. ልማት ማህበሩ ማዕድን የማምረት ፈቃድ ሲያገኝ ከፈቃድ ሰጪ አካል ጋር የገባውን በማዕድን ደንብና መመሪያ ላይ የተቀመጠውን የመንግስት ግዴታ ወጪዎችን ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ፣

7ኛ. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ/ በልማት ማህበሩ ስም በታወቀው ባንክ የተሰራ ሲፒኦ ብቻ ከሰነዱ ጋር አሽጎ መቅረብ አለበት፣

8ኛ. የጨረታ አሸናፊ በመሆን ከአሰሪው ድርጅት ጋር ውል ለገባው ጊዜ የሥራ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፣

9ኛ. የጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ከልማት ማህበሩ በሚገባው ጊዜ ገደብ የማምረት ስራ መጀመር አለበት፣

10ኛ. ለጨረታው የተዘጋጀው ቦታ 5 ሄክታር ይሆናል፡፡

11ኛ. ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችል አቅም ማሳያ በተከታታይ ስድስት ወር ውስጥ በድርጅቱ አካውንት ላይ ብር 20,000,000/ሃያ ሚሊዮን ብር / መኖሩን የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ የሚችል፣

12ኛ. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከዳውሮ ልማት ማህበር ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይቻላል፡፡

13ኛ. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ጨረታው ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 22ኛው ቀን ብሔራዊ በዓላት ወይም ሰንበት ላይ ከዋለ ለቀጣዩ የስራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

14ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝና የማይነበብ ካለ ተቀባይነት የለውም፡፡

15ኛ. ተጨማሪ ስለ ጨረታ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0473 45 02 58 /0917832352/0917832637 ይደውሉ፡፡

16ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።

 

የዳውሮ ልማት ማህበር

Save Tender