ተስፋ ለህይወት ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያገለገለ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ተስፋ ለሕይወት ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት
ያገለገለ የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ለህይወት ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያገለገለ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተሽከርካሪውን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ (የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ) አዲስ አበባ በሚገኘው ጀሞ 3 ፉሪ ኪና ሞል ህንጻ ቢሮ ቁጥር 306 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
-
- ለጨረታ የቀረበው ያገለገለ ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ገርጂ Nexus Hotel 100 ሜትር ገባ ብሎ በአካል በመገኘት የተሽከርካሪውን ሁኔታ ከላይ በተጠቀሰው ሥፍራ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ተገኝቶ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ለተሽከርካሪው ግዢ ተጫራቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ (የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ) ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ አስገብቶ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተመደበው ሰዓት ማስገባት ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ማቅረብ አለበት፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ወይም በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
- ጨረታው ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
- ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ፤ የሚቀርቡ ማናቸውም የመወዳደሪያ መጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታው የግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ የሚመለስላቸው ሲሆን፤ የጨረታው አሸናፊዎች ደግሞ፤ ያስያዙት ገንዘብ ከሚገዙት ንብረት ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠናቅቆ በመክፈል ተሽከርካሪውን አሸናፊነቱ ከተገለፀበት እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ድርጅቱ የራሱን አሠራር በመከታተል እርምጃ ይወስዳል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ተሽከርካሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ከስም ዝውውር ጋር በተያያዙ የሚደረጉ ክፍያዎችን፣ የመንግሥት ቀረጥና ታክስ እንዲሁም ማንኛውንም ተዛማጅ ወጪዎችን ይሸፍናል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 0911568004/ 0113805025/ 0913734566 አዲስ አበባ በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሱት የድርጅቱ አድራሻዎች በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ተስፋ ለሕይወት ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት
