Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-01 00:00:00
  • Categories Engineering Service

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ጀሞ ሚካኤል አጠገብ የሚገኘው የዋና መስሪያ ቤቱን የ"As-built Drawing” ሥራ ለማሰራት ሰነድ ላይ ባለው የሥራ ዝርዝር እና ቅድመ ሁኔታዎች (Evaluation Criteria) መሰረት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የአማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ጀሞ ሚካኤል አጠገብ የሚገኘው የዋና መስሪያ ቤቱን የ"As-built Drawing” ሥራ ለማሰራት ሰነድ ላይ ባለው የሥራ ዝርዝር እና ቅድመ ሁኔታዎች (Evaluation Criteria) መሰረት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የአማካሪ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

    1. የአማካሪ ድርጅት ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያለው፡፡
    2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል (የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የስራ ቀናትን ከሰኞ - አርብ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን::)
    3. ተጫራቾች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ ቲን፣ ቫት ፤ የንግድ ምዝገባ እና ሰነድ ይሸጥልኝ ማመልከቻ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
    4. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት በ22ኛው ቀን ሲሆን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
    5. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ /ተጫራቹ ጥሩ የመልካም ስራ አፈፃፀም ሪከርድ ከሌለው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
    6. ተጨማሪ ማብራሪያ ከድርጅቱ መረዳት ይቻላል፡፡
    7. ተጫራቾች በጨረታው ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

አድረሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ ሚካኤል አጠገብ የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና መ/ቤት “ OACf Buiiding" ላይ 6ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 12 ስልክ፡- 0912-08-00-80 / 0904-61-37-32

 

የኦሮሚያ ግብርና ኅ/ሥ/ማ ፌዴሬሽን ኃ/የተ/

Save Tender