Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 033 89 90 102
  • Website
  • Deadline01 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-01 00:00:00
  • Categories Construction Vehicle

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወጅት፣ ፣ በወፈለቅ እና በፈረስ ቤት ቀበሌዎች ያለውን የ17.95 ኪ/ሜ ኤክስካቫተር ጃካመር ያለው፣ ግሬደር ፤ ዳምፕ ትራክ /ሲኖ ትራክ/ ሮሎ በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መንገድ ማሰራት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2017

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወጅት፣ ፣ በወፈለቅ እና በፈረስ ቤት ቀበሌዎች ያለውን የ17.95 ኪ/ሜ ኤክስካቫተር ጃካመር ያለው፣ ግሬደር ፤ ዳምፕ ትራክ /ሲኖ ትራክ/ ሮሎ በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መንገድ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድና ምዝገባ ያለው/ያላት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ኤክስካቫተር ጃካመር ያለው፣ ግሬደር ዳምፕ ትራክ /ሲኖ ትራክ/ ሮሎ የማሽን አይነት ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 02 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በኢትዮጵያ ብሄራው ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of ciredt ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የእለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን እስከ 11:30 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 6 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም::
  10. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል።
  11. ማሽኑ የሚንቀሳቀስበት ሎቤድ ወይም ማጓጓዣውን አሸናፊው /ተጫራቹ ችሎ፡፡
  12. የማሽኑ ሰርቪስ ፣ የኦፕሬተርና ረዳት ወጪ ባለሀብቱ /ተጫራቹ ችሎ፡፡
  13. የማሸኑ ሰዓት መቁጠር ክፍያ የሚያስጠይቀው ስራ ቦታ ደርሶ ስራ ሲጀምር ብቻ ነው::
  14. ለማሽኑ የሚጠቀምበት ነዳጅ ፍጆታ አሸናፊው /ተጫራች/ ችሎ
  15. ለኦፕሬተሮች ረዳቶችና ነዳጅ ማመላለሻ መኪና ነዳጅ ወጪ አሸናፊው ተጫራቹ/ችሎ፡፡
  16. ጨረታው በሎት ነው፡፡
  17. ጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠው ሰዓት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334110386 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  20. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በአላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  21. በዚህ ውስጥ ያልተካተተ ካለ በግዥ መመሪያው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender