Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116250146
  • Website
  • Deadline24 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-24 00:00:00
  • Categories Water Construction , Building Construction

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት እቃዎችና ቁሳቁሶች ፣ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ለሠላ ድንጋይ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች የማጠናቀቂያ ግንባታ፣ ለወረዳው ውሃ ጽ/ቤት የምንጭ ውሃ ግንባታ በሙሉ ዋጋ በኮንትራክተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት እቃዎችና ቁሳቁሶች ፣ ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ለሠላ ድንጋይ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች የማጠናቀቂያ ግንባታ፣ ለወረዳው ውሃ ጽ/ቤት የምንጭ ውሃ ግንባታ በሙሉ ዋጋ በኮንትራክተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና (ከጀርባው ይመልከቱ የሚለው ኮፒ ተደርጎ መቅረብ አለበት) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና ይጠቅመኛል የሚሉትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የዕቃዎችን እና የሚገነቡትን የግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለሶስት ወር የተሰራ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፣
  7. ለውሃ ለሚገነቡ ግንባታዎች ደረጃ 8 እና በላይ በውሃ ነክ ስራዎች እና ለመማሪያ ክፍሎች የማጠናቀቂያ ግንባታ በግንባታ ዘርፍ የደረጃ 5 እና በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቁና አገልግሎት ተወዳዳሪዎች ለተከታታይ 16 ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል ። የውሃ ግንባታዎች ለተከታታይ 21 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በ21ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል :: የመማሪያ ክፍሎች የማጠናቀቂያ ግንባታ ለተከታታይ 31 ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል። ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ይከፈታሉ።

  1.  ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታ 10 ቀናት ለግንባታ ተወዳዳሪዎች ለተከታታይ 15 ቀናት ለግ/ን/አስ/ቡድን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  2.  በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ድጋፍ ይደረግላቸዋል፣
  3. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
  6. ስለሁሉም ጨረታዎች ተጨማሪ ማብራሪያና ማሻሻያዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ::

አድራሻ፡ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ፣

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender