Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-23 00:00:00
  • Categories Furniture

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 15/2017

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው::
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 - 6:00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ይከፈታል ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. ከላይ የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ሀዋሳ

Save Tender