የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ዕቃዎችን የጉምሩከ ክሊራንስ፣ የጭነት ማስተላለፍ እና የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶችን (Local Freight Forwarding Service Providers) በኮንትራት ስምምነት ለሶስት (3) አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ SSNT-T531
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ዕቃዎችን የጉምሩከ ክሊራንስ፣ የጭነት ማስተላለፍ እና የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶችን (Local Freight Forwarding Service Providers) በኮንትራት ስምምነት ለሶስት (3) አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በኢትዮጵያ ከላይ በተጠቀሰው የአገልግሎት ዘርፍ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግስት ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 04 ቀን 2017 ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T531 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
በጨረታው የሚካፈሉ ማንኛውም ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም:: አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ግንቦት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 - ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ: - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011 5178918
ኢ-ሜይል: EskedarG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
