የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ጋሻ ፕሮጀክት ግልጋሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን የግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር መሰፋ/ብ/ግ/ጨ/09/2017
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ጋሻ ፕሮጀክት ግልጋሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን የግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
01:- SANITERY MATERIALS, FIXTURES & FITTINGS
02:- PORCELAIN & CERAMIC FLOOR TILES
03:- PVC TILE & PVC SKIRTING & ADHESSIVE
04:- PAINTING MATERIAL
05:- GYPSUM PLASTER WORK... SUPPLY AND FIX
06:- QUARTIZE PAINT TO EXTERNAL WALL/ CONTEXTRA PAINTING..SUPPLY AND FIX
07:- WATER PROOF WORK... SUPPLY AND FIX
08:- GRANITE THREAD AND RISER & GRANITE WINDOW SILL & COPPING
09:- ARMSTRONG CEILING.....SUPPLY AND FIX
10:- FIRE HYDRANT CABINET WITH HOSE REELS AND 6KG FIRE EXTINGUISHERS
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ /VAT Registration Certificate/፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት የብቃት ሰርተፊኬት Tax clearance certificate እንዲሁም የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መ/ሰ/ፋ ግዥ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም በየሎቱ ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 መ.ሲ.ፋ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
- በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0115572734
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን
