የወልቃይ ጠገደ ሰቲት ሁመራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወልቃይት ወረዳ ፍርድ ቤት 800 ካ/ሜትር የሆነ ግንባታ ያረፈበት ቤትን በተመለከተ የወጣ ጨረታ ።
በወልቃይ ጠገደ ሰቲት ሁመራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወልቃይት ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ/ባለመብት ወ/ሮ ዛፈይ አለማው- ተወካይ ወ/ሮ ንግስት አለማው የፍርድ ባለዕዳ አቶ አታክልቲ ፋንታይ ሙሉ መካከል ስላለው የባልና ሚስት ንብረት አፈጻፀም ክርክር የፌዴራል የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት የልደታ 4ኛ ምድብ ችሎት በመ/ቁጥር 310001 በቀን 15/09/2016 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ እና በመ/ቁጥር 318767 በቀን 30/05/2017 ዓ.ም የተሰጠ የአፈጻፀም ትዕዛዝ ፣ አፈፃፀሙን የወልቃይት ወረዳ ፍርድ ቤት እንዲያስፈጽም በተሰጠው ውክልና መሰረት በአዲ ረመጥ ቀበሌ 03 ልዩ መጠሪያ “ፋንታይ ትዝታ ሆቴል” ተብሎ የሚጠራ አዋሳኙ በሰሜን ፀጋይ የማነብርሃን፣ በደቡብ መንገድ፣ ምዕራብ ዓ/ቃድር ሳሊህ፣ ምስራቅ ሽበሽ በጁ የሚያዋስን 800 ካ/ሜትር የሆነ ግንባታ ያረፈበት ቤት የጋራ የባልና ሚስት መሆኑ ተረጋግጦ ከተቻለ ግራ ቀኝ በአይነት እኩል እንዲከፋፈሉ ፣ በአይነት ለክፍፍል የማይመች ከሆነ በስምምነት ንብረቱን በማስገመት የግምቱን ግማሽ አንዱ ለሌላ በመክፈል ንብረቱን እንዲያስቀር፣ በዚህም ካልተስማሙ በስምምነት ሽጠው ገንዘቡን እኩል እንዲካፈሉ፣ በዚህም ካልተስማሙ በፍርድ አፈጻጸም ተሽጦ ገንዘቡን እኩል በማለት የተሰጠን ውሳኔ የፍርድ ባለዕዳ በቅደም ተከተል መሰረት ፍርዱ ቀርበው ቀነ ቀጠሮ እንዲፈጽሙ ፣ በአካል ወይም በህጋዊ ተወካይ አማካኝነት እንደ ፍርዱ ቀርበው የማይፈጽሙ ከሆነ የማይፈፅሙበት ህጋዊ ምክንያት ቅርበው እንዲያስረዱ በማለት ከዚህ ውጭ በተሰጠው ቅደም ተከተል መሰረት መብትዎ አውቀው ካልቀረቡ ውሳኔው የፍርድ ባለዕዳ በሌለበት ፍርዱ የሚፈጸም መሆኑ በማለት ቀጠሮ ለ17/08/2017 ዓ.ም - 3:30 ሰዓት 1ኛ ችሎት የፍርድ ባለዕዳ እንዲቀርቡ ሲል የወልቃይት ወረዳ ፍርድ ቤት አዟል፡፡
በወልቃይ ጠገደ ሰቲት ሁመራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወልቃይት ወረዳ ፍርድ ቤት
