Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline21 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-21 00:00:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ በ2017 በጀት አመት ባቀዱት መሠረት የሀዋሳ ከተማ ቄራ አገልግሎት የስጋ ማመላለሻ ኮንቴነር መኪናዎችን ብዛታቸው 6 /ስድስት/ የሆኑትን ውጫዊ አካል Body /Van/ እና ውስጣዊ አካል Alminium Sheet በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ በ2017 በጀት አመት ባቀዱት መሠረት የሀዋሳ ከተማ ቄራ አገልግሎት የስጋ ማመላለሻ ኮንቴነር መኪናዎችን ብዛታቸው 6 /ስድስት/ የሆኑትን ውጫዊ አካል Body /Van/ እና ውስጣዊ አካል Alminium Sheet በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ጋራዦች መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዘጋቢ የሆኑ ፣
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
  4. የጋራዥ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሠርተፊኬት ከመን/ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የታደሰውን ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ::
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡45 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መም⁄ያ

 

Save Tender