በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ /ለ2ኛ ጊዜ/ ፡ ሎት 2 የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር፣ ሎት 3. የምግብ ምርቶች/ በኮንትራት ውል አቅርቦት/ ፣ ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ /ለ2ኛ ጊዜ/ ፡ ሎት 2 የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር፣ ሎት 3. የምግብ ምርቶች/ በኮንትራት ውል አቅርቦት/ ፣ ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ የቫት ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 በማስገባት ደረሰኙን በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጥቅል ዋጋ ለሎት 1. 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ፣ ለሎት 2. 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 3. 3000.00/ ሶስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 4 ብር 700.00 /ሰባት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 ላይ ገቢ አድርጎ ሰነዱን ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን፣ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ እነዳድ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ግቢ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀንና እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነም በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓቱ ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡ በጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች በተላላፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ወጭውን በመሸፍን እነደድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤ ለሁሉም ሎቶች ለውል መያዣ የሚፈለጉ ወጭዎችን አሸናፊው አካል የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ለወጣው ወጭ መ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ውድደሩ የሎት 1 በነጠላ ዋጋ፤ የሎት 2 እና 3 በጥቅል ዋጋ ስለሚታይ ተጫራቾች በአንድ ሎት ያሉትን ዝርዝር እቃዎች ሁሉንም ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ግዥ ፈጻሚው አካል ካወጣው ስፔስፊኬሽን ውጭ በራሱ ስፔስፊኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሙያ የሚጠይቁ እቃዎች በሚመለከተው ባለሙያ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ እነ/ወ ሲ/ሰ/ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በአካል ወይም በስልክ ቁጥራችን 0913271823 /0946088403 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
