በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።
ስለሆነም ያገለገሉ ንብረቶች በመሸጥ የሚወገዱ የንብረት አይነቶች
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
|
1 |
ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበር |
|
2 |
ያገለገሉ የካፌ ጠረጴዛ |
|
3 |
ያገለገሉ ካውንተር |
|
4 |
ያገለገሉ ኮመድኖ |
|
5 |
ያገለገሉ ጠረጴዛ |
|
6 |
ያገለገሉ የእጅ መታጠቢያ በርሜል |
|
7 |
ያገለገሉ የእንጨት ኮት መስቀያ |
|
8 |
አዲስ የመፀዳጃ ቤት ሲንክ |
|
9 |
ያገለገሉ የመስታወት ሼልፍ |
|
10 |
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ |
|
11 |
ያገለገሉ ሙሉ ቆርቆሮ |
|
12 |
ያገለገሉ ማከፋፈያ |
|
13 |
ያገለገሉ የመስመር የስልክ ቀፎ |
|
14 |
ያገለገሉ የወረቀት መብሻ |
|
15 |
ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ ትንሹ |
|
16 |
ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ ትልቁ |
|
17 |
ያገለገሉ ስቴፕለር መምቻ መካከለኛ |
|
18 |
ያገለገሉ የእጅ ባትሪ ትልቁ |
|
19 |
ያገለገሉ የእጅ ባትሪ ትንሹ |
|
20 |
የመኪና ልብስ ያገለገለ |
|
21 |
የተሰባበረ ፕላስቲክ ወንበር |
|
22 |
ያገለገሉ የሰርቭር ቦክስ |
|
23 |
ያገለገሉ ሂተር (ማሞቂያ) |
|
24 |
ያገለገሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ |
|
25 |
ያገለገሉ የውሃ ማጣሪያ |
|
26 |
በአይጥ የተበላ የቆሻሻ ቅርጫት ፕላስቲክ |
|
27 |
ፒፒሲ ባለ 20 |
|
28 |
ያገለገሉ ፍሪጅ (inesit) |
|
29 |
ጃንቦ የቢራ መጠጫ ብርጭቆ |
|
30 |
የሲንግል ቢራ መጠጫ ብርጭቆ |
|
31 |
የሀበሻ ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
32 |
የዋልያ ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
33 |
የአምቦ ውሀ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
34 |
የፕፕሲ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
35 |
የሜታ ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
36 |
ባለ ዛፍ አረቄ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
37 |
አዋሽ የወይን ጠጅ ጠርሙስ |
|
38 |
የራያ ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
39 |
ኮካ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
40 |
የጊዎርጊስ ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
|
41 |
የዳሸን ቢራ ጠርሙስ ከነሳጥኑ |
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የሰጠው ዋጋ በሚሞላው አምድ ስር ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በፖስታ አሽገው በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ ወይም ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በአዲስ አበባ መርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 705 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይገባል።
- ማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሰነዱን ገዝቶ መዉሰድና የሚወገዱ እቃዎች ላይ በጨረታ በመግዛት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት አጠገብ ወይም ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በሚገኘው መርካቶ ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ታሽጎ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ለእያንዳንዱ ቁጥር ለተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት” (Addis Ababa City Government Revenues Bureau Merkato No.2 M/T/P/Branch Office) ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ፖስታ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ ጠዋቱ 04፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ንብረቱ የሚሸጠው አሁን ባለበት ሁኔታ ይሆናል።
- ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ 7ኛ አከባቢ ድሬ ህንጻ ጎን ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ባለው ስቶር ይሆናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 011 276-9862-/011 273-2771 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
