በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በም ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 2 የመኪና ጎማዎች እና ሎት 3 የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የመድሃኒት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ለመግዛት ይፈልጋል።
የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 04/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በም ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
ሎት 2 የመኪና ጎማዎች
ሎት 3 የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የመድሃኒት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል።
- ማንኛውም የእቃ አቅራቢና የስራ ተቋራጭ ከላይ ለተዘረዘሩት የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የመድሃኒት ቤት G+1 ግንባታ ደረጃ 5 እና በላይ ለሆኑ BC/GC እና ተጫራቾች መካከል አወዳድሮ ማሰራት መግዛት ይፈልጋል።
- የተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣ የግንባታ የምስክር ወረቀት ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከከልሉ የስራና ከተማ ልማት ቢሮና ከወረዳ ተቋማት ማቅረብ የሚችሉ፣ የመልካም ስራ አፈፃፀምና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከብር 200000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ተጫራቾች ለግንባታ ስራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና ማሸነሪዎችን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መስራት የሚችል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገውና ማህተም አድርገው ያቅርቡ። የሚፈለገው ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታው ላይ ዋናውንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተው ማቅረብ ለባቸው። እንዲሁም በሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ ገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት። ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1፡- 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት3፡ 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር ብቻ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታው ጋር ለብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸማ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ስራ የጽሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ለሎት1 እና ሎት 2፣ 100 (አንድ መቶ ብር)፣ ለሎት 3፡ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 06 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የመድሃኒት ቤት ለG+1 ግንባታ ጨረታ ለ30 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ለእቃ አቅርቦቱ ደግሞ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን።
- ስራውን ለመስራት ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ የግንባታ ስራውን ለመስራት ለሎት3፡- ውሉ ላይ በሚገለፀው ቀን መሰረት ሲሆን ለመኪና መለዋወጫ እቃዎች እስከ ሰኔ 30/10/2017 ዓ ም ድረስ ሲሆን ለመኪና ጎማዎች እቃ አቅርቦት ደግሞ በ15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቹ ከከልላችንም አልፎ በወረዳችንም ግንባታ የማጓተት ወይም የማቋረጥ ችግር የሌለበት እና የመልካም ስራ አፈጻጸሙ የተረጋገጠ መሆን አለበት።
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- የተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% (25%) ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ እና ውል መያዝ ይኖርበታል።
- ማሳሰቢያ፡- ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ግዜ ለግንባታው ስራዎች 60 /ስልሳ ቀናት ሲሆን ለእቃ አቅርቦት ደግሞ 40 /አርባ ቀናት መሆኑን መገንዘብ አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 247 0509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን
