የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ “ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ ፣ ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ደማ/02/2017
የጨረታ ዙር፡ 2ኛ
የጨረታ ዓይነት፡ መደበኛ
-
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ “ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ ፣ ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፤ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን። በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
-
የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
-
የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ነው።
-
ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
-
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
-
ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማኘት ይቻላል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም የተጠበቀ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
