Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 26 79 91 07
  • Website
  • Deadline16 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-16 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Furniture

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የሥራ ሂደቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የአሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 2ኛ የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት


 

  ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የሥራ ሂደቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ የአሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 2ኛ የቢሮ ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ የኮምፒዩተር እና ተዛማጅ ዕቃዎች የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ስዓት ድረስ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦሪጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ሞልተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ ደረሰኝ 1% ቢል ቦንድ በመቁረጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቹ በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።

6. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታ ውድድሩ እንደ አስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል።

8. ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ክፍት ቦታ ላይ የዕቃውን ሞዴል ፣ ብራንድ /መለያ/ የተመረተበትን ሀገር አካተው መሙላት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ጥራት ያለውና ኦሪጅናል ዕቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል ነገር ግን ተመሳሳይ ፎርጅድ ዕቃዎችን ቢያቀርቡ ለሚመጣው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ 09 26 79 91 07 / 0935 31 70 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአብክመ ጠ/ፍ/ቤት በ/ሰ/ሸ/ዞን ከፍ/ቤት የሚዳ ወረዳ ፍ/ቤት

  

Save Tender