በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 የህትመት ስራዎች፤ ሎት 2. የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድኃኒት፤ በግልፅ ጨረታ አወዳዳሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ጽ/ቤት ወረዳ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ
ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 የህትመት ስራዎች፤ ሎት 2. የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድኃኒት፤ በግልፅ ጨረታ አወዳዳሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O. ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
የሎት ቁጥር |
የእቃ ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
|
ሎት 1 |
የህትመት ስራዎች |
ብር 3,000.00 |
|
ሎት 2 |
የህክምና መገልገያ መሳሪያ እና መድኃኒት |
ብር 10,000.00 |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 405 እየቀረቡ መግዛት ይቻላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 303 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽገው 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብት የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች የድጋፍ (የዋስትና) ደብዳቤ ከተሰጠበት አካል ደብዳቤው በፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ የፀደቀ እና የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ ቲተር ያለው መሆን አለበት፤ ከዛ ውጭ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ከአያት አደባባይ አራብሳ ኮንዶሚኒየም በሚጭኑ ታክሲዎች ተሳፍረው ትምህርት ቤት ማዞሪያ የሚለው ቦታ ላይ በመውረድ ማግኘት ይችላሉ
ስልክ ቁጥር +251-11 6124-407
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ጽ/ቤት ወረዳ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ
