የጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር የደረቅ ጭነት አገልግሎት ገልባጭ መኪና ባለበት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
የመኪና ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር የደረቅ ጭነት አገልግሎት ገልባጭ መኪና ባለበት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
-
የተሸከርካሪው አይነት 190×30 ሞዴል ፊያት /FIAT/ 79.4 ኩንታል የሚጭን ባለ 6 ጎማ የሚገኝበት ቦታ መሃል ሜዳ ከተማ ከማህበሩ ጽ/ቤት ሲሆን ማናቸውም ተጫራች ከቦታው በመግኘት መመልከት ይችላል፡፡
-
የጨረታው መነሻ ዋጋ 15 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ሆኖ እያንዳንዱ ተጫራች በሰጠው ዋጋ 2% የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 ከፍለው መሃል ሜዳ ከማህበሩ ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ በስልክ ቁጥር 09-44-66-66-68 በማነጋገር መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች ሂሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መሃልሜዳ በማህበሩ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ 22/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በሚቆጠር በ10 ቀን ውስጥ እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው:: 11፡35 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋል፡፡
-
በሰነድ አቀራረቡ ላይ ስርዝ ድልዝ አይፈቀድም፡፡
-
ተጫራቾች አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
-
የጨረታ ሰነዱ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
አሸናፊው ተለይቶ በደብዳቤና በፋክስ በደረሰው አምስት ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያውን 10% ከፍሎ ውለታውን መፈፀም ይኖርበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውለታውን ካልፈፀመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
-
የንብረቱ የስም ማዛወሪያና የዘመኑ ቦሎ ቀሪ ክፍያዎችን ገዥው ይሸፍናል፡፡
-
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በአካል ወደም በስልክ ቁጥር፡- 011-6-85 -01-07/ 09-22-46-54-80/ 09-44-66-66-68 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጓሳ ኢንዱስትሪያል ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
