በአፈ ከሣሽ እነ ወ/ሪት ብስራት ወ/አማኑኤል እና በአፈ ተከሣሽ እነ ወ/ሮ ፋሲካ ፍቅሩ መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በደ/ብርሃን ከተማ በድሮው አጠራር ቀበሌ 09 ክልል ውስጥ አዋሳኙ በምስራቅ ሲሳይ ተፈራ፣ በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን አቶ መስፍን፣ በደቡብ ቃልኪዳን እንግዳሸት የሚያዋስነውን የካርታ ቁጥር 0726 በ163 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ ከሣሽ እነ ወ/ሪት ብስራት ወ/አማኑኤል እና በአፈ ተከሣሽ እነ ወ/ሮ ፋሲካ ፍቅሩ መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን የሟች አስር አለቃ ወ/አማኑኤል ተክለወልድ የውርስ ንብረት የሆነውን በእነ ብዙነሽ ሀይሌ ስም የተመዘገበውን በደ/ብርሃን ከተማ በድሮው አጠራር ቀበሌ 09 ክልል ውስጥ አዋሳኙ በምስራቅ ሲሳይ ተፈራ፣ በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን አቶ መስፍን፣ በደቡብ ቃልኪዳን እንግዳሸት የሚያዋስነውን የካርታ ቁጥር 0726 በ163 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በግምት መነሻ ዋጋ 1,196,420.71 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ ሃያ ብር ከ71/100 ሳንቲም) ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ስለዚህ፦
-
ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እና የጨረታው አሸናፊ እደታወቀ ወዲያውኑ ያሸነፉበትን 1/4ኛውን በፍ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ ሲፒአ ለሃራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
-
ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው የውርስ ሀብት ድርሻን ለማከፋፈል ነው፡፡
-
ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
-
የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
